Tender Detail

Tender Details

  • Company ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0911678567
  • Website
  • Deadline28 Jul 2026, 5:00 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-07-29 09:00:00
  • Categories Vehicle

ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ


ያገለገሉ መኪኖች ሽያጭጨረታ ማስታወቂያ


ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተሸከርካሪዎቹን ለመግዛት የምትፈለጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩ መስፈርቶች መሰረት ጨረታው ላይ እድትሳተፉ እናሳውቃለን፡፡

የጨረታ መስፈርቶች፡-

1)
ማንኛውም ተጫራች ለቀረበው ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን 10% /አስር በመቶ/ በባንከ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ በሚል ማስያዝ አለባቸው፡፡
2)
ተጫራቾች ሕጋዊና የታደሰ የ2018 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡
3)
ለጨረታ ሠነድ ጠመንጃ ያዥ ባንከ /ቴሌ ገራዥ/ ፊት ለፊት በሚገኘው ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ እህት ኩባንያ ኦሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ የኋላ ወርቅ ህንፃ በመገኘት 200 ብር በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
4)
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውንና /የመታወቂያ ኮፒ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5)
ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ 100% እና 15% ተ/እ/ታከስ ያካተተና የሚያቀርቡትም ዋጋ በኢትዮጵያ ብር መሆን ይኖርበታል፡
6)
ተጫራቾች ዋጋ ለመሙላት በተዘጋጀው ዝርዝር ቅፅ ላይ ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡
7)
ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡
8)
የተሸከርካሪዎቹን ዝርዝር ሁኔታ በአካል ለማየት ከፈለጉ በቅሎ ቤት ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ እና ዱከም መጋዘን ውስጥ ከሰኞ አስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00-10፡00 ድረስ ማየት ትችላላችሁ፡፡
9)
አሸናፊው ተጫራች በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ባያነሳ ያስያዘው ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡ ከአሸናፊነት ተሰርዞ ድርጅቱ የራሱን አዋጪ መንገድ በመጠቀም መኪናዎቹን የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
10)
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
11) ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውም የስም ማዛወሪያ ወጪ ይከፍላል፡
12)
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት ተጫራቾችድርጅቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ዋና ሰነድ /Bid document/ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በድርጅቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስ.ቁጥር-0911678567/ 0966257146/ 0921797181/ 0930033441
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ

Save Tender