ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ በባሌ ጎባ ከተማ የምጀኝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የባሴ ትራንስፖርት፤ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ
ድጋሚ የወጣ የጩረታ ማስታወቂያ
የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ህዳር 02 ቀን 1957 ዓ.ም. የተቋቋመ ቢሆንም ማህበሩ ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ በንግድ ስራ ላይ አለመኖሩን ሰነዶች ያመለከታሉ፡፡ በአባላቱ ለፍርድ ቤት በቀረበ አቤቱታ ማህበሩን እንደገና ለማደራጀት ያልተቻለ በመሆኑ ሁኔታውን ለአባላቱ ቀርቦ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተደረገ መደበኛ እና አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ በአባላቱ አብላጫ ድምጽ ማህበሩ እንዲፈርስ ተወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት የማህበሩ ሂሳብ የማጣራት ስራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በሂሳብ ማጣራቱ ሂደትም ከማህበሩ አባላት በቀረበ ጥያቄ መሰረት የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አከስዮን ማህበር ንብረት የሆነ 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ በባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ይህን ንብረት ባለበት ሁኔታ ማህበሩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከላይየተዘረዘረውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 በባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር ስም በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር01322240761900 ገቢ በማድረግ አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ከማህበሩ ቢሮ ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል፤
1) ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በራሱ ወጪ ባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ በመገኘት መመልከት የሚችል፣
2) በጨረታው ለመሳተፍ ብር 50000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይንም በማህበሩ ስም የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ ማስያዝ የሚችል፤
3) በጨረታው አሸናፊ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ / ድርጅት በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ሙሉ ከፍያውን በመክፈል ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በአሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በıo (አስር) ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ እና ኃላፊነት ማንሳት የሚችል፤
4) በጨረታ ሰነዱ መሰረት የሚገዛበትን ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም ባንክ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ሰነድ በአንድ ላይ በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን አ.አ. ሜከሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር506 በመገኘት ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ21 (ሃያ አንድ) ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚችል፤
5) ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከቀኑ በ06፡00 ሰዓት የሚዘጋ ይሆናል፡፡ ጨረታው በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ይከፈታል፡፡
6) ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7) ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 313167 /0911 127265 (አቶ ዘሪሁን ደጀኔ) ወይንም 0911 679969 (አቶ ንጉሴ) በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት
የባሴ ትራንስፖርት፤ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ
