Tender Detail

Tender Details


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ለፈንድ ማጠናከሪያ እንዲሆን ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የኤሌከትሮኒክስ እና የቢሮ መገልገያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን


የጨረታ ማስታወቂያ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ለፈንድ ማጠናከሪያ እንዲሆን ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የኤሌከትሮኒክስ እና የቢሮ መገልገያዎች nacታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 400.00 አራት መቶ ብርነበሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኤፍ አካውንት ቁጥር1000332121708 እየከፈሉ ከተቋሙ ግዢና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ አዲስ አበባ ከተማ ቲዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፣ በአስረኛው ቀን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሚል ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ አሸናፈዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍለው ሲመጡ ተመላሽ ይሆናል፤ለተሸጠፉት ተጫራቾf የጨረታ ግምገማ ውጤት በጨረታ አዕዳቂ መፅደቁ ወይም ውድቅ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላ ሲፒአ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10 ቀናት ሆኖ በ10ኛው ቀን ጨረታው 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛኑ ቀን 8፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡

4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመግዛት ከሰነዱ ላይ ሙሉ ዝርዝሩን ያገኛሉ፡፡

5. የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 608 በመገኘት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

6. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁት ንብረቶች የሚገኙበት ቦታ CMC የተባበሩት አደባባይ አካባቢ ደርግ የሰራቸው ኮንዶሚኒየም ውስጥ እና ሜከሲኮ ጠማማ ፎቅ ቤዝመንት እና ልደታ ፍርድ ቤት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።

ስተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-558-24-37/ 011-558-23-76 /09-01-19-09-39/09-61-71-26 04

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባስስልጣን

Save Tender