Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Insurance Company S.C (ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ቦሌ ወሎ ሰፈር ወደ ወንጌላዊት ህንጻ በሚወስደው መንገድ ቴሌ ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ሊዲያ አስናቀ ህንፃ ላይ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን 2ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 68 73 41
  • Websitehttps://oromiainsurance.com/
  • Deadline26 Jun 2026, 5:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-06-27 09:00:00
  • Categories Vehicle , Vehicle Spare Parts

ኩባንያችን የሙሉ ውድመት ካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኩባንያችን የሙሉ ውድመት ካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 . ለመሸጥ ይፈልጋል

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪዎቹ እና ሌሎች ቁሳቁሶች በሚገኙበት ቃሊቲ ሸዋ ዳቦ ጀርባ ለሞን ብሎኬት ማምረቻ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያችን ሪከቨሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰኔ 10 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ሰኔ 19 ቀን 2018 . በመመልከት የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ቦሌ ወሎ ሰፈር ወደ ወንጌላዊት ህንጻ በሚወስደው መንገድ ቴሌ ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ሊዲያ አስናቀ ህንፃ ላይ በሚገኘው ዋና /ቤታችን 2 ፎቅ በመግዛት ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰኔ 18 እና ሰኔ 19 ቀን 2018 . እስከ ቀኑ 1100 ድረስ ገቢ በማድረግ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

Ø ጨረታው በኩባንያው ዋና /ቤት 3 ፎቅ ላይ በሚገኘው የሥልጠና አዳራሽ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 300 ሰዓት ላይ የውስጥ ኦዲት አገልግሎት እና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፣

Ø ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

Ø ተጫራቾች ለተሽከርካሪ የሚጫረቱ ከሆነ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 15% ወይም በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በባንክ ክፍያ ማስያዣ (CPO) በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነዋጋው ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ የተሽከርካሪ አካላት የሚጫረቱ ከሆነ የጨረታ መነሻ ዋጋቸውን መሠረት በማድረግ ኩባንያችን ባስቀመጠው ዝርዝር መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

Ø ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ከጨረታ በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪዎች በሙሉ ገዢው ይሽፍናል፡፡

Ø የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪ ይከፍላሉ፡፡

Ø አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በኩባንያው የማስታወቂያ ቦርድ እና ድረ ገጽ ላይ የሚገለጽ ሲሆን፣ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡

Ø የተለያዩ የተሽከርካሪ አካላት እና ቁሳቁሶችን የሚጫረቱ እና አሸናፊ የሚሆነ በምድብ የተቀመጡትን ቁሳቁሶች ከኩባንያው የሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወጪ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

Ø ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ .

ዋና /ቤት

አድራሻ፡- ወሎ ሰፈር ቴሌ ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ሊድያ አስናቀ ህንፃ

በስልክ ቁጥር 09 11 68 73 41/09 57 08 01 05 ወይም

0115-57-21-48

Save Tender