Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ
  • Address , Phone: 0917826584
  • Website
  • Deadline24 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security25,000.00
  • opening date2026-06-24 14:15:00
  • Categories Pharmaceutical Products

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች እና የሰራተኛ ቤተሰቦች የመድኃኒት አቅርቦት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት ውል በመዋዋል ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ


ብሔራዊ ግስፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር RE-LP/OT/23/SIG/2018


1.
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች እና የሰራተኛ ቤተሰቦች የመድኃኒት አቅርቦት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት ውል በመዋዋል ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

2.
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብርመክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ከሊራንስ⁄ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች/አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

3.
ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡



የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው ስልሳም ጨስስቅ ህንፃ ፊት ሰፌት፣
ፈሊፒስ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220

ስልክ ቁጥር +251 115 51 62 71 ወይም 011550 04 17
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ


4.
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

5.
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በከፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ከቴክኒከ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6.
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይመሆን ይኖርበታል፡፡

7.
የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል፡፡

8.
ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡



የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

Save Tender