Tender Detail

Tender Details

  • Company የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
  • Address ኡዴ ደንካካ 7.5 ኪ.ሜ ፒስታ መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251-114-338-822
  • Website
  • Deadline07 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1%
  • opening date2026-07-07 10:30:00
  • Categories Office Supplies And Services , Metals And Metal Working , Electronics Materials , Vehicle

ጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የማይጠቀምባቸውን የተለያዩ ብረታ ብረቶች፤ ተሸከርካሪዎች፤ የቢሮ እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተለያዩ ኬሚካሎች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2018

 

ተቋማችን ጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የማይጠቀምባቸውን የተለያዩ ብረታ ብረቶች፤ ተሸከርካሪዎች፤ የቢሮ እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተለያዩ ኬሚካሎች አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ከላይ ለተገለጹት ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

2.     ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በመንግሥት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ -ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በተቋማችን ጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግብይትና ሽያጭ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 20 የሥራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት ክፍያ በመፈፀም በ20 ቀናት ውስጥ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።

6.     ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

7.     የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ21ኛ (ሃያ አንደኛው) ቀን 4:30 ላይ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ይከፈታል።

8.     የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡ ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ስልክ ቁጥር:- +251-114-338-822      +2519-20-01-78-38

አድራሻ ኡዴ ደንካካ 7.5 ኪ.ሜ ፒስታ መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

 

ጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ

Save Tender