Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ
  • Address , Phone: 0582221127
  • Website
  • Deadline30 Jun 2026, 2:30 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security500,000.00
  • opening date2026-06-30 15:00:00
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ከብሔራዊ ዋሽ ኘሮግራም በተገኘ የበጀት ድጋፍ የውሃ መመርመሪያ ኪት በግልዕ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ከብሔራዊ ዋሽ ኘሮግራም በተገኘ የበጀት ድጋፍ የውሃ መመርመሪያ ኪት በግልዕ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ለመወዳደር የተጋበዙ መሆኑን እያሳወቅን ፡-

1.
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2.
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርብ፡፡

3.
ከላይ በተራ ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.
የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።

5.
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና የሚያስይዝ፤ ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ጠቅላ ዋጋ ከ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ መብለጥ የለበትም ።

6.
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትርበስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7.
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤

8.
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም በ 8:30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል።ሆኖም ዕለቱ የሥስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡

9.
ሌሉች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

10.
ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

11.
የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሽነፈውን የውሃ መመርመሪያ ኪት የጨረታ ሰነዱ ላይበተቀመጠው አግባብ አብክመ ጤና ቢሮ ንብረት እስቶር ላይ ማቅረብ አለበት፡፡

12,
በጨረታው የተወዳደረ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር / በመከፈል ከቢሮው የሰነድ ሽያጭ ከፍል መውሰድ ይችላል ፡፡

13.
ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14.
ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር 058-222-1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Save Tender