በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን የህክምና መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በየካ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የእንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ 003/2018
በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን የህክምና መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
⁕ ሎት 1. የህክምና መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች ግዥ
በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች በሙሉ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድና የፌዴራል ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር መኖራቸውን ማረጋገጫ ደብዳቤ፣ የቫት ተመዝጋቢና ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከጤና ጣቢያው ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ለጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር) ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
4. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ እንደተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ በፖስታ በማሸግ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናል እና ኮፒ እሽግ ለያይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ኮፒ የለሌው ኦርጅናል ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
5. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
6. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሲሆን በ6ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ጤና ጣቢያው ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው።
8. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡- በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ቤላ ወይም ጣሊያን ኤምባሲ ጎን የሚገኝ ሲሆን
ለበለጠ መረጃ
⁕ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
ስልክ ቁጥር 0913 60 56 32 ወይም 0913 66 67 47
በየካ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የእንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
