የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስሪያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና የማሻሻያ (ማዘመን) (Bid for Vending Machine Repair and Upgrade) ስራዎችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጫረታ ማስታወቂያ
የጫረታ ቁጥር:-SSNT-T615
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ዋና መስሪያ ቤት) የሚገኙ የሽያጭ ማሽኖች የጥገና የማሻሻያ (ማዘመን) (Bid for Vending Machine Repair and Upgrade) ስራዎችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
1. በሽያጭ ማሽኖች የጥገና ፤ የማሻሻያ (ማዘመን) እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት 1 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥርSSNT-T615 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) "በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ሀምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
አሸብር ተሾመ በስልከ ቁጥር: +251-115-17-49-18 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ኢ.ሜ.ል:- ashebirte@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
