Tender Detail

Tender Details


ግዮን ሆቴሎች ድርጅት ሎት 1 የሠራተኞች የደንብ ልብስ ሥራ ጨርቆች አቅርቦት /ከነእጅ ሥራው/ ሎት 2 የሙቅ ውሃ ፓምፕ ግዥ ሎት 3 የቴሌቪዥንና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና

Ghion Hotel


የግዮን ሆቴሎች ድርጅት

ሎት 1 የሠራተኞች የደንብ ልብስ ሥራ ጨርቆች አቅርቦት /ከነእጅ ሥራው/

ሎት 2 የሙቅ ውሃ ፓምፕ ግዥ

ሎት 3 የቴሌቪዥንና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና

ከላይ በሎት ለተገለፁት ዝርዝር መሠረት ዕቃዎች የአገልግሎት ግዥ ማቅረብ የሚሉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  • የ2018 በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
  • Tin No /የግብር መለያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ያለው
  • Vat/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያለው
  • በገቢዎች ሚኒስቴር የጨረታ ፈቃድ /ክሊራንስ/ ያለው፤
  • የተጠቀሱትን የአገልግሎት እና የዕቃ ግዥ በማቅረብ ልምድ ያላቸው፤
  • ለሎት 1 የደንብ ልብሱ ሥራ በአጠቃላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያወጣውን ደንብ ያከበረ መሆን አለበት፤
  • በሚወዳደሩባቸው የጨረታ ዘርፎች ለሚያቀርቡት ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፤
  • የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በዋናው እንግዳ መቀበያ በመክፈል ለእያንዳንዱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115513222 Ext. 5429/5163 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • የሥራ ሰዓት፡ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00 – 6፡00

ከሰዓት 7፡00 – 11፡00

አርብ ጠዋት ከ2፡00 – 5፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Save Tender