Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ
  • Address , Phone: 0115159548
  • Website
  • Deadline17 Jun 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-06-17 09:30:00
  • Categories Wood And Wood Working , Electrical Materials

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2018 በጀተ ዓመት በመስሪያ ቤቱ አገልግሎት ሊሰጡ ማይችሉ የተለያዩ የፍሎረሰንት ማቀፊያዎች፣ አምፖሎች፣ ጣውላዎች፣ ወንበሮች፣ ጋዜጣዎች፣ ምንጣፎች፣ መጋረጃዎችና … ወዘተ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ


ያገለገሉ ዕቃዎች ግልፅ የጨረታ ሽያጭ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በ2018 በጀተ ዓመት በመስሪያ ቤቱ አገልግሎት ሊሰጡ ማይችሉ የተለያዩ የፍሎረሰንት ማቀፊያዎች፣ አምፖሎች፣ ጣውላዎች፣ ወንበሮች፣ ጋዜጣዎች፣ ምንጣፎች፣ መጋረጃዎችና … ወዘተ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች የእቃዎችንን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በብር 200 (ሁለት መቶ) በመግዛት እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

⁕    ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

⁕    ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሰነድ ማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ /10/ አስር ቀናት ውስጥ በግዥ ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

⁕    ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት፣ በማህተም በማረጋገጥ እና በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የቴክኒካል ሰነድና ፋይናንሻል ሰነድ በማለት ለይተው ማቅረብ ሲኖርባቸው ይህንኑ መረጃ ከገዙት ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።

⁕    አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው አቅርቦት መጠን 25% በላይ መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል፡፡

⁕    ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በማስገባት በ11ኛው ቀን 3፡00 ሶስት ሰአት ተዘግቶ 3፡30 (ሶስት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እለት ይከፈታል፡፡

⁕    ቢሮው ጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ሜክሲኮ ሰነዱ የሚሸጠው ፊሊፕስ ህንፃ አጠገብ ፍትህ ቢሮ ህንፃ ከፌዴራል ፖሊስ ወረድ ብሎ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ህንፃ 4ኛ ወለል ላይ ይሆናል፡፡

ስልክ፡- 011515954

ማሳሰቢያ፡-  ተጫራቾች ዕቃዎቹን በአካል በመገኘት ማየት ይኖርባቸዋል።

 

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ

Save Tender