በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ሲዳማ የጭሬ ወረዳ አስተዳደር/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደዉ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ሲዳማ የጭሬ ወረዳ አስተዳደር/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደዉ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች በሙሉ እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
1. በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ከደረጃ 5 እና ከዝያ በላይ ፍቃድ ያላቸው ሆነው መጸዳጃ ቤት ሥራ ላይ ከዚህ በፊት የሠሩበት የስራ ልምድ ያላቸው።
2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደርኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ መመዘግባቸውን የሚያሳይ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾቹ ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት /ቴክኒክ/ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና /ኦርጅናል/ ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው። ይህ ተጣርተው ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክረው ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ /bid security/ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና /bank guarantee/ ወይም የክፍያ ማዘዣ /cpo/ ከመጫራቻ ሰነድ ወይም የቴክኒካል ዶክመንት ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የሥራ ቦታ /site/ በራሳቸው ወጭ አይተው /Vist/ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፍቃዳቸው እና ተ.ዕ.ታ /VAT/ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ19/አስራ ዘጠኝ/ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 1,600 /አንድ ሺህ ስድስት መቶ/ ብር በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ሲ) ጭራ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመከፈል ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ፡፡
7. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልተው ጨረታ ማስከበሪያ /bid bond /security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና /ኦርጅናል/ እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ /ሁለት/ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በትልቁ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁለቱም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጭሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለዚሁ አግልግሎት የተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው የቴከኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
2. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ 0910740670/0926064520
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
