Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም
  • Address በሰሜን ወሎ ቅ/ላሊበላ ደብረ ዘይት ቀበሌ ከደብሩ አዲሱ ጽ/ቤት (መካንዝባ) ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-336-0021
  • Website
  • Deadline11 Jun 2026, 4:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityከሚጫረቱበት ዋጋ 10%
  • opening date2026-06-11 04:30:00
  • Categories Vehicle

የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት በስሙ ተመዝግበው የሚገኙትን ተሽከርካሪ መኪናዎች በሕጋዊ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም


የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት በስሙ ተመዝግበው የሚገኙትን ተሽከርካሪ መኪናዎች በሕጋዊ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1.     ሚኒባስ ( አባ ዱላ) 1

2.     ምኒባስ (5 L) 1

3.     ኃይሉክስ (ዳብል ካፕ) 1

4.     ኤንትሪ ቦት የተጫነበት 1

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መኪናዎች በጨረታ መግዛት ለምትፈልጉ በተጫራች በኩል መሟላት ያለበት መሥፈርት፡-

የጨረታ ሰነድ ሽያጭ

➢ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ከደብሩ ጽ/ቤት መግዛት አለባቸው።

➢ ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸዉ።

➢ የመግዣ ዋጋ በአንድ መኪና ለብቻ ወይም በጠቅላላ ሊቀርብ ይችላል ፖስታ ላይ የገንዘቡ መጠን በግልጽ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለበት፡፡

የጨረታ ሰነድ አቀራረብ

➢ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን በታሸገ ፖስታ (ኢንቨሎፕ) በተጠቀሰው አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

➢ ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡

➢ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ጨረታው ይከፈታል ፡፡

➢ በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

➢ ሰነዱ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

የቴክኒክ ሁኔታ

➢ ተሽከርካሪዎች አሁን ላይ ባሉበት ሁኔታ የሚሸጡ ሲሆን ገዳሙ ከሽያጭ በኋላ ለሚፈጠረው ማንኛውም የቴክኒክ ችግር ተጠያቂ አይሆንም፡፡

➢ ከጨረታ በፊት ቴክኒካል ሁኔታ ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን የባለሞያ ክፍያ በተጫራች በኩል ይሆናል።

➢ ተወዳዳሪዎች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መኪናዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡

የክፍያ ሁኔታ

➢ አሸናፊ ተጫራች የቀረበውን ገንዘብ ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 100% በገዳሙ አካውንት የመክፈል ግዴታ አለበት።

<< ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር >>

 

ማሳሰቢያ፡- የገዳሙ ሰበካ ጉባኤ አስ/ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 033 336 00 21 (09 11 78 81 86) ይደውሉ

አድራሻ ቅ/ላሊበላ ደብረ ዘይት ቀበሌ ከደብሩ አዲሱ ጽ/ቤት (መካንዝባ)

 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም

Save Tender