የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የኪራይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/11/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የኪራይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
• ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
• ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEP Transmission Substation Construction Account No. 1000252665203 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-19 ትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 14 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
• ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን የኪራይ አገልግሎቶች በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/11/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
• ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የኪራይ አገልግሎቶች ግዥ መወዳደር ይችላሉ።
|
የአገልግሎት ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ባለ 10 ቶን ሃፍ ክሬን እና ባለ 40 ጫማ ሃይቤድ ከባድ ጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ |
ብር 100,000.00 |
ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት |
• ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
• ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116732190 መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
