በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተቋሙን Analog X-ray machine ጥገና በማድረግ ወደ Digital X-ray machine ለማስቀየር ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተቋሙን Analog X-ray machine ጥገና በማድረግ ወደ Digital X-ray machine ለማስቀየር ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ለስራው አስፈላጊውን ማቴርያል በማቅረብ መስራት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚታሟሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በዘርፉ የተሰማራ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት
2. በ2018 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል /የሚትችል
3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል /የሚትችል
4. ቫት /ቲአት ተመዝጋቢ የሆነ/ች
5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው/ያላት
6. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የሚትችል
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ C.P.O ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታ ሰነድ በብር 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15 ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት ተከታታይ የመንግስት የሥራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር -6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ጨረታ የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ባይገኙ ጨረታውን መከፈት አያዳግትም፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0967811275/0913070604/0919703532/0912804638/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ህዝባዊ በዓል ባለበት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ የሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል
