Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline02 Jun 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር
  • opening date2026-06-02 14:00:00
  • Categories Construction Works , Contractors

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሁሩታ፣ ዲክሲስ፣ ጎንዴ፣ መቂና በገላን የሕንጻ ማሳመር ሥራ፣ የጥበቃ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤትና የአጥር ሥራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሁሩታ፣ ዲክሲስ፣ ጎንዴ፣ መቂና በገላን የሕንጻ ማሳመር ሥራ፣ የጥበቃ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤትና የአጥር ሥራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

RFQNo. 4283724,4283801,4283786,4283770, እና 4283800 ቅደም ተከተል ፡፡

በዚሁ መሠረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ሕጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማኅበር ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

መስፈርት

1.     ጨረታው ከግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤

2.     ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የሥራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።

6.     ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

7.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።

8.     መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን

 

Save Tender