Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline02 Jun 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ብር
  • opening date2026-06-02 14:00:00
  • Categories Advertising And Promotion

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሪጅኑ ሥር የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉትን የማስታወቂያ ሥራዎችን በማስታወቂያ ዘርፍ የተሰማሩትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሪጅኑ ሥር የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉትን የማስታወቂያ ሥራዎችን በማስታወቂያ ዘርፍ የተሰማሩትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

RFQ No. 4283857

በዚሁ መሠረት በማስታወቂያ የሥራ ዘርፍ የተሰማራችሁ፤ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ እንድ ዓመት የሥራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማኅበር ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ከፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

መስፈርት

1.     ጨረታው ከግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤

2.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብርየከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች ከዚህ በፊት በማስታወቂያ ዘርፍ የሠሩበትን የሥራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።

6.     ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

7.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።

8.     መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡  

ኢትዮ ቴሌኮም

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን

Save Tender