Tender Detail

Tender Details


የሰበታ አግሮ ኢንዱሰትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዓለምገና ሰበታ መንገድ ላይ  የሚገኘውን የወተት ማቀነባባሪያ ተቋም የጥበቃ አገልግሎት ለሚሰጥ ብቁ ድርጅት በዝግ ጨረታ አወዳድሮ የጥበቃ ሥራውን በአገልግሎት ግዥ መስጠት ይፈልጋል፡፡

Sebeta Agro Industry


የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የሰበታ አግሮ ኢንዱሰትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዓለምገና ሰበታ መንገድ ላይ  የሚገኘውን የወተት ማቀነባባሪያ ተቋም የጥበቃ አገልግሎት ለሚሰጥ ብቁ ድርጅት በዝግ ጨረታ አወዳድሮ የጥበቃ ሥራውን በአገልግሎት ግዥ መስጠት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፤ የሚከተለውን ዝርዝር በማሟላት በዚሁ ሥራ የተሠማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች መሣተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ድርጅቱን በአካል በመጎብኘት ለጥበቃ ሥራው የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ደረጃና ብዛት አጥንቶ በማቅረብ ፣
  3. የመድን ዋስትና እንዲሁም በቂ የሱፐርቪዥን ተሽከርካሪ መኖሩን ማረጋገጫ በማቅረብ፣
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አሥር ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ፣
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ሰነዶቻችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አለምገና ሰበታ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ በሚገኘው ዋናው óብሪካ በአካል በመቅረብ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ – ስልክ ቁጥራችን 0925-11-61-66

        ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ ማህበር(ማማ ወተት)

 

 

Save Tender