ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር በሰንጠረዥ የተገለፁትን Office Furniture እንዲሁም ለዋና መ/ቤት ህንፃ የዲጅታል ማስታወቂያ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Tsedey Bank S.C
|
|
ፀደይ ባንክ/አ.ማ/ Tsedey Bank (S.C) | |||
| የጨረታ ማስታወቂያ | ||||
| የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0014/2018 |
ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር በሰንጠረዥ የተገለፁትን Office Furniture እንዲሁም ለዋና መ/ቤት ህንፃ የዲጅታል ማስታወቂያ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት-1 ፡- Office Furniture
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | ብዛት | ተ.ቁ | የእቃው አይነት | ብዛት | |
| 1. | Officer/Medium Back Swivel Arm Chair | 200 | 5. | Clerical Table 120*60*75 | 100 | |
| 2. | Fixed Gust Chair with arm rest | 300 | 6. | Three –Seater Guest Chair | 70 | |
| 3. | Managerial Table with Drawer 180*90*75 | 49 | 7. | Notice Board | 100 | |
| 4. | Managerial /High Back Swivel Arm Chair | 49 | 8. | Group Table | 6 |
ሎት-2 ፡- ለዋና መ/ቤት ህንፃ የዲጅታል ማስታወቂያ ለማሰራት
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ በጨረታ ለመካፈል /ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ/ ሊኖራቸዉ ይገባል።
- ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ የ90ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115581658
ፀደይ ባንክ አ.ማ
