Tender Detail

Tender Details


ለመጽደቅ የዘለቄታ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ዙሪያ በሚገኙ 4 የፕሮጀክት ሳይቶች ላይ የ4 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ ግንባታ እና የውሃ ምርታማነት ሙከራ ስራዎችን ብቃት ባላቸው ተቋራጮች ለማሰራት ይፈልጋል።

LEMETSDEK Charity Organization


          የጨረታ ማስታወቂያ

የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ / Deep Well Drilling Project /

ቦታ፦ በደብረ ብርሃን እምዬ ምኒሊክ ክፍለከተማ ፣ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቀበሌ፣ ቦራሌ ቱሉ አምባ እና ጠንቆሌ የገጠር ንዑስ ቀበሌ

ለመጽደቅ የዘለቄታ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ዙሪያ በሚገኙ 4 የፕሮጀክት ሳይቶች ላይ የ4 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ ግንባታ እና የውሃ ምርታማነት ሙከራ ስራዎችን ብቃት ባላቸው ተቋራጮች ለማሰራት ይፈልጋል።

  • ለመፅደቅ ሳይት፦ 1 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ (ከ160-180 ሜትር)።
  • የቦራሌ፣ የጠንቆሌ እና የቱሉ አምባ መንደሮች፦ 3 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች (ከ140-160 ሜትር)።

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የሚከተሉትን ህጋዊ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፦

  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የዘመኑ የግብር ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰነድ።
  • ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የደረጃ 5 (WWC/WWD-5) እና ከዚያ በላይ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት።
  • በመንግስት የጨረታ እገዳ (Debarment) ውስጥ ያልተካተቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ጨምሮ ) ዘወትር በስራ ሰዓት መተው የማይመለስ00 (አምስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት ታሽጎ፣ በዛው ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡ አያት ዞን አምስት መንገድ 14

+251976572397 / +251913610673

tojustify24@gmail.com / info@lemetsdek.com

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 

Save Tender