Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-2-20-20-77
  • Website
  • Deadline25 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-25 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ቢሮን ለማስጠገን ይፈልጋል።

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ቢሮን ለማስጠገን በታቀደው መሠረት ግዥውን ለመፈጸም እንዲቻል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ሕጋዊ ፊቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1.     በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ፤

2.     በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4.     አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

5.     የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 30 (ሰላሳ) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20/ሃያ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችው በ500 (አምስት መቶ ብር) ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 120,000 (አንድ መቶ ሀያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመስከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡

7.     ጨረታ ሰነዱ በስም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፕ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ተከታታይ ቀናት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቢሮ ቁጥር 30 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8.     ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 30 ይከፈታል፤ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

9.     ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና በሀዋሳ ከተማ አስተዳዳር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳዳር አይችልም። ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

10. በጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲከ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል 5% (ከአምስት ፐርሰንት በላይ ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡

11. ለጨረታ ያሰገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአስራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር የቀረበው ዋጋ ከ20% በላይ በሆነ መጠን ያነሰ እና ከ30% በማይበልጥ መጠን ያነሰ ሲሆን እንደተስበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል። ከ30% በላይ ያነሰ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unit Cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።

13. በጨረታ ማስታወቅያና በጨረታ ሰነድ ላይ ልዩነት ከተፈጠረ በጨረታ ሰነድ ላይ ያለው ይወስዳል።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462202077

 

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት

Save Tender