Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በሰ/ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-664-16-12
  • Website
  • Deadline12 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-12 00:00:00
  • Categories Pharmaceutical Products

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለቀወት ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለቀወት ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የእንስሳት መድሃኒት

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1.     በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3.     በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የግዥው መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4.     በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾች ከ1-4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.     በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታው ውድድሩ በጥቅል መሆኑን አውቀው ጨረታውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

7.     ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8.     ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው በሎትı የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ጸንቶ ከሚቆይበት 40 ቀን በኋላ በተጨማሪ 20 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9.     በሎት 1 ተወዳድረው የሚያሸንፋ ተጫራቾች 10% የውጩ ማስከበሪያ በማስያዝ መዋዋል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አቅርቦቱን ላከናወኑበት ክፍያ ሲጠይቁ በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቁባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይለስ ብር 200 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡

11. ማንኛውም ተጫራቶች ከላይ በተገለጸው በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033-664-16-12 ማግኘት ይችላሉ።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender