Tender Detail

Tender Details

  • Company ህብረት በካስማ የጋራ ህንፃ የቤ/ባ/ማህበር
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline06 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-06 00:00:00
  • Categories Construction Works

ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ቫርኔሮ በሚባለው አካባቢ የሚገኙትን ባለ አምስት ወለል አምስት ህንጻዎች የውጭ እድሳት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ህብረት በካስማ የጋራ ህንፃ የቤ/ባ/ማህበር


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ቫርኔሮ በሚባለው አካባቢ የሚገኙትን ባለ አምስት ወለል አምስት ህንጻዎች የውጭ እድሳት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ ደረጃ ሰባት እና በላይ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ፈቃድ እና የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ለዚህ ሥራ የተጠሩት ተጋባዥ ተጫራቾች

1.     የሥራ ልምዳቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ እንዲያቀርቡ ይፈልጋል፡፡

2.     ለዘመኑ የታደሰ የንግድና ሥራ ፍቃድ ምዝገባ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ደብዳቤ ጋር በቀረበው የሥራ ዝርዝር መሰረት ለቀረቡት ሥራዎች የማቴሪያል እና የእጅ በአንድነት አካቶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ከማህበሩ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡30) ከሚያዝያ 19 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺ) በሲፒኦ ወይም በቢድ ቦንድ መልክ አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማህበሩ ጽ/ቤት በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከማቅረባቸው በፊት ህንጻዎቹ ያሉበትን ሁኔታ በአካል በመቅረብ እንዲጎበኙ ይመከራል፡፡ ተጫራቾች ለቴክኒክ ምዘና የሚያስፈልገውን የተሟላ ሰነድ በተለይም ከዚህ ቀደም ያከናወኑትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም የሚገልጹ ሰነዶችን ከህጋዊ የሥራ ፈቃድ ሰነዶች ጋር አያይዘው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኤንቨሎፕ ውስጥ ከጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ጋር በኤንቨሎፕ በማሽግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የዋጋ ማቅረቢያው (ፋይናንሻል ፕሮፖዛል) በሌላ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ አሰሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

 

ህብረት በካስማ የጋራ ህንፃ የቤ/ባ/ማህበር

Save Tender