የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ የዝርያ ማሻሻያ ሆርሞን (Prostaglandin Hormone በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ
በድጋሚ የወጣ የዝርያ ማሻሻያ ሆርሞን /prostaglandin hormone/ ግልጽ የጨረታ ማ/ቁጥር 136/18
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ የዝርያ ማሻሻያ ሆርሞን (Prostaglandin Hormone በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የዕቃው ዓይነት
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
የሚታሸግበት ሰዓት
|
የሚከፈትበት ሰዓት
|
|
1
|
የዘርያ ማሻሻያ ሆርሞን (Prostaglandin Hormone)
|
ዶዝ
|
30,000
|
40,000
|
9:00
|
9:05
|
በመሆኑም በንግዱ ሥራ ዘርፍየታደሰ ፈቃድ ፤የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ45 ቀናት የፀና መሆን ይኖርባታል።
በተጫራቾች የሚያቀርባው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና እና በጥሬ ገንዘብ ያስያዙባትን ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጠባት ቀን 10/08/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 ለሰነድ በመክፈል ዱራሜ ከተማ በሚገኛው ክልል ግብርና ቢሮ ቁጥር 003 መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 19/08/2018 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዶችን በአንድ ፖስታ በማዘገጃት በቢሮው ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
የጨረታው ሳጥን 19/08/2018 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሸጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫረቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 003 ይከፈታል።
ቢሮው ለዚህ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 046-554-1461 ይጠቀሙ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ
