Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አውቶብስ ተራ ወደ መሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112768120
  • Website
  • Deadline23 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-23 00:00:00
  • Categories Generators , Computer Laptop And Accessories , Office Machines And Computers

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል።

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2018

 

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል።

ሱት 1፡- ኮምፒዩተር………………………………… የጨረታ ማስከበሪያ ብር 159600.00

ሱት 2- ጀኔሬተር………………. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80000.00

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

*         የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ የሚያቀርብ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፡፡

*         በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

*         በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ሲሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ በጽ/ ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም መወዳደርየሚችሉት በራሳቸው በተመረተ ምርት ብቻ ይሆናል።

*         ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቁጥር 2 ለዚህ ተብሎ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

*         ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት አስቀድሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ሳምፐል የሚያስገባ ተወዳዳሪ በአስራ አንደኛው ቀን ቢያመጣ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

*         ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡ 30-10፡00 ሰዓት ድረስ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

*         ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

*         ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለo/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በዘኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

*         ተጫራቾች የገዛችሁትን ሙሉ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡ ሙሉ ሰነዱን ያላያያዘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።

*         የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስያዣ ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ 10% (ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ማስያዝና ተዋውለው እቃዎቹን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

*         የግዥ ውል በሚፈፀምበት ወቅት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ሊቀንስ ይችላል።

*         ተጫራቾች በመንግሥት ግዥ ዌብሳይት ላይ ድርጅታችሁ ተመዝግቦ መገኘት አለበት።

ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: -0112768120/0112303241/0112303054 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

ስድራሻ፦ አዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ወረዳ 8 አውቶብስ ተራ ወደ መሳስሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ የካቲት 23 ስጠቃሳይ ሁስተኛ ደረጃ ት/ቤት

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የካቲት 23 አጠቃሳይ ሁስተኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender