Tender Detail

Tender Details

  • Company ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 212 5402
  • Website
  • Deadline01 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-01 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሲዳማ ብሔራዊ ከልል መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት ሊያሰራ ላቀደው የቦና ዙሪያ ወረዳ የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ከልል መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት ሊያሰራ ላቀደው የቦና ዙሪያ ወረዳ የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1.     ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2018 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡

2.     አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ

3.     በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡

4.     የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብታት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው! ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

5.     የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

6.     የሥራ ተቋራጮች በተጫራቶች መሠረት ህጋዊ መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ስርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶከመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ፋይናንስ ከፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

7.     የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የማንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።

8.     የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ቴክኒካል ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድረሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡

9.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።

10. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

 

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

Save Tender