Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሐል አምባ
  • Address ጉራጌ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113360162
  • Website
  • Deadline24 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-24 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው መንገድ ት/ል/ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ከሰሪ እስከ ከቢር ሀሚድ መስጂድ፣ ከሲሪ እስከ አረዳ ገበያ ድረስ ላለው መንገድ የጠጠር ሥራና የስትራክቸር ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሐል አምባ


ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር GGWW/006/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው መንገድ ት/ል/ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ከሰሪ እስከ ከቢር ሀሚድ መስጂድ፣ ከሲሪ እስከ አረዳ ገበያ ድረስ ላለው መንገድ የጠጠር ሥራና የስትራክቸር ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ፡-

1.     የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፣ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2.     በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ይዘው መምጣት አለባቸው።

3.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መሐል አምባ ከተማ ገ/ጉ/ ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

4.     የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC/Rር ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች

5.     የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብቻ በገ/ጉ/ወ ወ) ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው::

6.     ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሃያ ) ተከታታይ ቀናት መሐል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር -03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7.     የጨረታው ሰነድ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8.     መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ማሳሰቢያ 1. በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም ::

2. በወረዳው ውስጥ ፕሮጀክት ይዞ ሥራውን ያልጨረሰ ተጫራች እና በውክልና ሰነድ ገዝቶ መወዳደር አይችልም።

3. ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሠሪው መሥሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው

 

ለበለጠ መረጃ:- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ

ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ይደውሉ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

መሐል አምባ

Save Tender