Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰ/ሰ/ሀ/ል ፅ/ቤት
  • Address እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስ/አዲሱ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115-58-28-71
  • Website
  • Deadline14 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-14 00:00:00
  • Categories Equipment And Accessories , Equipment

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰ/የሰ/ሀ/ል/ፅ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰ/ሰ/ሀ/ል ፅ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 05/2018

 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰ/የሰ/ሀ/ል/ፅ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል።

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1 የደንበኞች ወረፋ ማስያዣ ከነሙሉ እቃው እና አክሰሰሪው

ሲፒኦ ብር 20,000

                                                                   

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።

1.       የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት በአቅራቢነት የተመዘገቡ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር / TIN NO/ የተጨማሪ እሴት ታከስ ሰርተፍኬት ያላቸው።

2.       የጨረታው ሰነድ አቀራረብ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና የፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ ለየብቻው እንዲሁም ሲፒኦ /CPO/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለበት።

3.       በጨረታው ላይ ጥቃቅንና አነስተኛ ይበረታታሉ ሆኖም ግን የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለመግኘት የሚችሉት ከተቋማት የበላይ ሀላፊዎች ቲተርና ፊርማ ተገቢውን የተሞላ ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ነው።

4.       ናሙና የሚያስፈልጋቸው ማቴርያሎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል።

5.       ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ ማስገባት ይኖርበታል።

6.       የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ የፐብሊከ ሰ/ሰ/ሀ/ል/ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚከፈተው ደግሞ ከ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።

7.       አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስረከቢያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት።

8.       መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.       ሰነድ መግዣ 400 ብር በድርጅቱ አካውንት ቁጥር 1000001455293 ቂርቆስ ክ/ከተማ አቅም ግንባታ ፅ/ቤት ብላችሁ ገቢ እንድታደርጉና የገቢ ደረሰኛቸውን ብቻ ይዛችሁ በማቅረብ አገልግሎቱን እንድታገኙ እናሳውቃለን።

አድራሻ ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስ/አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ስልከ ቁጥር 011 558-2871

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰ/የሰ/ሀ/ል ፅ/ቤት

Save Tender