Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ኢ/ክ/መ/ጋሞ ዞን ሰላም በር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት
  • Address ጋሞ ዞን ሰላም በር ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0964962986
  • Website
  • Deadline24 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-24 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Construction Works

በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ አ/ስር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከተማ አስተዳደሩ በከተማ ውስጥ ጎርማና ዳንባዪ ቀበሌ የመንገድ ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ እንዲታወጅ ይፈልጋል፡፡

በደ/ኢ/ክ/መ/ጋሞ ዞን ሰላም በር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ አ/ስር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከተማ አስተዳደሩ በከተማ ውስጥ ጎርማ ና ዳንባዪ ቀበሌ የመንገድ ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ እንዲታወጅ ይፈልጋል፡፡

•        1ኛ ዲች ግንባታ ሥራ 538ሜ

•        2ኛ ጠጠር ንጣፍ ሥራ 2.244 ኪ ሜ

ስለሆነም በመንግሥት ግዥ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት፡-

1.     የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

2.     የዘመኑ ግብር የተከፈለበት

3.     የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/

4.     ቫት ተመዝጋቢ ከሆነ መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል

5.     ከሽያጭ ዋጋ ላይ የመንግሥት ግብር 3% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ

6.     የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት

7.     የደ/ኢ ክልል ወይም ፌዴራል ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው ደረጃቸው GC/RC 8 እና ከዚያ በላይ ያላቸው

8.     አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችን መሣሪያዎችን በግላቸው አጓጉዘው መሥራት የሚችሉ

9.     E-G-P ምዝገባ የተመዘገቡበትን ፕሪንት አርጎ ማቅረብ የሚችሉ

10. ማንኛውም ተጫራች ከወድድር በፊት የሥራ ሳይቱን በራሱ አይቶ የሳይት ምልከታ መረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት

11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ዋና እና ፋይናንሻል ዋና እንዲሁም ኮፒ በመለየት በተለያየ ፖስታ በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በታሸገ ፖስታ በሠ/በርከ/አ/ፋ/ጽ/ቤት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

12. የተጫራቹ ዋጋ የሂሳብ ስህተት ከእርማት በኋላ ከ3% በላይ ወይም በታች መሆን የለበትም

13. በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላው ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 15% ማስያዝ አለበት፣

14. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 22 /ሀያ ሁለት/ ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡

15. ተጫራቾች የሥራ ዝርዝር የሚገልጸውን ሰነድ በሳይት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ ቀናት ሠ/ከ/አ/ፋ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናል፡፡

16. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ ዋሰትና የሚመለስ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ CPO የባንክ ማህተም በስተጀርባ በማስደረግ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

17. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ22ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡

18. ጨረታው የሚከፈተው በ23ኛው ቀን 4፡00 ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።

19. ተጫራቾች ወይም የተጫራቹ ወኪል ባለመገኘት ጨረታውን መከፈቱን አያስተጓጓልም፡፡

20. 23ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለበት ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

21. ድርጅቱ/ተጫራቹ መሐንድሶች 1. ሳይት መሐንዲስ 2. ቀያሽ መሐንዲስ በፊት የጸደቀ ውልና ተከታታይ የሥራ ግብር የተከፈለበት የአራት ወር ፔሮልና የካሽ ደረሰኝ ከገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከመዋሉ በፊት ያለውን ማቅረብ የሚችል

22. ከመሐንዲስ ግመታ 15% ከፍ ዝቅ ካለ ተቀባይነት የለውም፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ

1.     ጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

2.     ድርጅቱ/ተጫራቹ በተለያዩ ክሶችና የሥራ እገዳ የተጣለባቸው መወዳደር አይችሉም፡፡

ሞባይል ቁጥር፡- 0964962986/0984689747

 

በደ/ኢ/ክ/መ/ጋሞ ዞን ሰላም በር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት

Save Tender