ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሰሚት በተለምዶ ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙትን G+4 ሕንፃ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 750 ካ.ሜ እና G+2 ሕንፃ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 442ካ.ሜ ያላቸው ሕንፃዎችን ባሉበት ሁኔታ ለተለያዩ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Ethio Engineering Group (ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር፡ ኢኢግ/ግቢዴ/ብግጨ/004/2018
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሰሚት በተለምዶ ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙትን G+4 ሕንፃ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 750 ካ.ሜ እና G+2 ሕንፃ ጠቅላላ ቦታ ስፋት 442ካ.ሜ ያላቸው ሕንፃዎችን ባሉበት ሁኔታ ለተለያዩ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመስከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው ወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣
2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ወይም የቲኦቲ ተመዝጋቢ ፍቃድ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
4. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
5. ተጫራቹ የሀገር ውስጥ፣ የዓለም አቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ የርዳታ ድርጅት (NGO) ወይም የሲቪክ ማኅበራት ከሆነ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
6. ተጫራቹ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፍቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የግሩፑ ዋና መሥሪያ ቤት ብሎክ "C” የግብይትና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜክሲኮ ቅርንጫፍ በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000028606177 በመክፈል እና የክፍያ ደረሰኙን በማቅረብ ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መውሰድ ይችላሉ።
|
የሎት ቁጥር |
የሎት መጠሪያ ስም |
የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
ሎት 1 |
ለሆቴል፤ ለሆስፒታልና ክሊኒክ፣ ባንክና፣ ኢንሹራንስ፣ ለሱፐር ማርኬት፣ ለዘመናዊ ቢሮዎች፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለትምህርት ቤት፣ ለገስት ሃውስ፣ ለመኖሪያ ቤት፣ ለተለያዩ ምርት ማሳያዎች እንዲሁም ለመሳሰሉት አገልግሎቶች |
500 |
50,000.00 |
|
ሎት 2 |
ለሆስፒታልና ክሊኒክ፣ ለዘመናዊ ቢሮዎች፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለትምህርት ቤት፣ ለገስት ሃውስ፣ መኖሪያ ቤት እንዲሁም ለመሳሰሉት አገልግሎቶች |
500 |
50,000.00 |
8. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ የኪራይ ዋጋ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እና ፋይናሽያል ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻቸው ማስገባት አለበት፡፡
9. ተጫራቶች የተጠቀሱትን ሰነዶች በመግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሕንፃዎቹን መመልከት ይችላሉ።
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡
11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው መዋዋል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ውሉን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ተዋውሎ ካልጨረሰ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለግሩፑ ገቢ ይደረጋል፡፡
12. ግሩፑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይሆናል።
13. ግሩፑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር +251986333388 ወይም +251986333344 ደውሎ መጠየቅ ይችላል ::
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ
