በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ውሃ ጽ/ቤት አማካኝነት ሰፍራ ሹማ ቀበሌ ንጽህ መጠጥ ውሃ ታንከር ግንባታ እና የመሎ ኮዛ ልማት ማኅበር ቅ/ጽ/ቤት ሞደል የማኅበረሰብ አቀፍ የመድኃንት መደበር ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ፕላን ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
• ሎት አንድ ውሃ ጽ/ቤት አማካይንንት ለፍራ ሹማ ቀበሌ ንጽህ መጠጥ ውሃ ታንከር ግንባታ
• ሎት ሁለት የመሎ ኮዛ ልማት ማኅበር ቅ/ጽ/ቤት ሞደል የማኅበረሰብ አቀፍ የመድኃኒት መደበር ግንባታ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ውሃ ጽ/ቤት አማካኝነት ሰፍራ ሹማ ቀበሌ ንጽህ መጠጥ ውሃ ታንከር ግንባታ እና የመሎ ኮዛ ልማት ማኅበር ቅ/ጽ/ቤት ሞደል የማኅበረሰብ አቀፍ የመድኃንት መደበር ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ከታች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፤
2. የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤
3. ከግብር ሰብሳቢ መሥርያ ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
4. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው/ያላት፤
5. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች፤
6. የታደሰ የሙያ ፈቃድ GC ወይም BC ለውሃ WWC ከደረጃ (1-7) ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
7. መልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
8. የግንባታ ቦታ የጎበኙበት ደብዳቤ ከአሠሪው መ/ቤት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
9. የአውራቢዎች ስም ዝርዝር ወስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማሰረጃና ሌሎች ሠነዶችን ከጨረታ ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
10. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ በቸክ በመሎ ኮዛ ወረዳ ፈ/ጽ/ቤት ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነድ ጋር አንድ ላይ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመሎ ኮዛ ወረዳ ገብዮች ጽ/ቤት በመክፈል ሠነዱን ከግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይኖርበታል።
12. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የግንባታ ሥራው የመወዳደሪያ ሃሳብ ደጋፍ ሠነዶች በግልጽና በጥራት የሚታይ እና የሚነበቡ መሆን አለባቸው። ይህም የሚሆነው ከላይ በተገለጸው መሠረት ሆኖ ከተገለጹት ጉዳዮችና ሁኔታዎች ጋር የተጣጠመና ተቀባይነት ያላቸው መሆን አለባቸው የማይነበብ እና የማይታዩ መረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
13. ተጫራቾች ከላይ ከ1-12 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘውትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል።
14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት አንድ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ21ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በ21ኛው ቀን 3፡30 ይከፈታል። ሎት ሁለት ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ21ኛው ቀን 4፡30 ታሽጎ በ21ኛው ቀን 5፡00 ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
– መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
– ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 09 16 76 70 44 ወይም 09 10 40 95 44 ይደውሉ።
መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
