Tender Detail

Tender Details

  • Company የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት
  • Address አየር ጤና ታክሲ ተርሚናል ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-35-74-96
  • Website
  • Deadline13 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-13 00:00:00
  • Categories Construction Works

በኮልፌ ቀራንዩ ክ/ከተማ የአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት በአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚሰራ የጥገና ስራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት


የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡005/2018

 

በኮልፌ ቀራንዩ ክ/ከተማ የአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት በአየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚሰራ የጥገና ስራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው እስፈሳጊ የሆኑ ግብአቶችን እና የተሟላ የሰው ሀይል በማቀረብ በተጠቀሰው ቀናት ሙስጥ ስራውን ማጠናቀቀ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የስራ ቦታ

ወረዳ

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

ተቋራጭ

1

አየር ጤና 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚያሰራው ጥገና ስራ

04

ለደረጃ GC7/BC6 እና ከዚያ በላይ 60,000 ብር

ደረጃ GC7/BC6 እና ከዚያ በላይ የሆነ ተቋራጭ

30 ቀን

 

1.     ለስራው የንግድ ምዝገባ እና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑ ግብር የ2016 ዓ/ም የከፈሉ፣ የ2017 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ከገቢዎች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፤ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::

2.     ተጫራቾች የጨረታ ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሽያል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ፊርማ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሽያል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመፃፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡

3.     ተጫራቾች ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት በቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃቸውን ኦርጂናል (original) እና የማይመሰስ ኮፒ ይዞ (copy) በመቅረብ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የስራ ቀናት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 11ኛው የስራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

4.     ተጫራቾች ለ 30 ቀናት የሚያገለግል ይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or SECURITY) በባንክ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (UNCODITIONAL BANK GUARANTEE) በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለበት።

5.     ተጫራቾች በጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቀተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ስራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቾቹ የዋጋ ትንታኔ (COST BREAK DOWN) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፤ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከስራው ጋር ያልተመጣጠነ (UNBALANCED RATE) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

6.     ተጫራቹ በጨረታ ያስገባው ፋይናንሽያል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned rate correction) እና ነጠላ ዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for rate correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ይሰረዛል።

7.     በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነፃ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያን በሚያዘው መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ከሚሰራው ስራ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ከመንግስት ተቋማት ማቅረብ የሚችል፡፡

 

የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት አየር ጤና ታክሲ ተርሚናል ፊት ለፊት ስልክ 0118357496/01188387908

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የአየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት

Save Tender