የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለስካይ ላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የመፀዳጃ ቤት ወረቀት /Roll Tissue toilet paper/ አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T606
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለስካይ ላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የመፀዳጃ ቤት ወረቀት /Roll Tissue toilet paper/ አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
1. የለስላሳ ወረቀቶች እና ተያያዥ ምርቶች የሀገር ውስጥ አምራች የሆነ፣
2. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ ሁለት (2) ዓመት እና ከዛ በላይ የሥራ ልምድ ያላውዉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T606 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፡-
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-89-18
ኢ-ሜይል: ESAYASIS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
