በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በህንፃ ስራ ተቋራጭ BC እና ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ GC ደረጃ 8 እና በላይ በህብረተሰብ ተሳትፎ በጀት ለአዳዲ ቀበሌ ለሩክሲ ቀበሌ ለጎልባ ቀበሌ ለፊጦ ቀበሌ ለጠንገጉ ቀበሌ እና ለቡራ ቀበሌዎች የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 10/2018
ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በህንፃ ስራ ተቋራጭ BC እና ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ GC ደረጃ 8 እና በላይ በህብረተሰብ ተሳትፎ በጀት ለአዳዲ ቀበሌ ለሩክሲ ቀበሌ ለጎልባ ቀበሌ ለፊጦ ቀበሌ ለጠንገጉ ቀበሌ እና ለቡራ ቀበሌዎች የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ፦
1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TN No/ ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግንባታዎች የሚሳተፋ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገበ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
2. ግንባታውን በውለታው ጊዜ ውስጥ በአይነት በመጠን በጥራት ሳያጓድል መገንባት የሚችል።
3. ስራውን በተሰጠው ማስረጃ /ዲዛይን መሰረት ሰርተው ማጠናቀቅ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ግንባታ 13,000 /አስራ ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ በ አን/ጠ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በመሂ 1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት። የግንባታ ግዥ ስለሆነም ተጫራቹን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግንባታውን አድራሻ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በዚሁ እለት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
7. 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል።
8. በማንኛውም ግዥ ለግንባታዎች ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 /አስር ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።
10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ግንባታ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው የስራ ዝርዝር መሰረት በውሉ መሰረት ሰርቶ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
11. የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰአት ለእያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር መግዛት ይችላሉ።
12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል።
13. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት ደብረብረሀን መስመር ላይ ነው።
15. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-6 32-01-47 ወይንም 011-6-32-00-19 ደውለው ይጠይቁ።
በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
