Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን
  • Address ሰሜን ወሎ ዞን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0333311597
  • Website
  • Deadline17 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-17 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming

የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን ለሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ፡ በራያ ቆቦ ወረዳ 01 ቆቦ ዙሪያ ቀበሌ ለሚያሠራው የንጋት መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የመስኖ መሰረተ ልማት ከደረጃ 3 እና በላይ ያሉትን WWC ሥራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን ለሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ፡ በራያ ቆቦ ወረዳ 01 ቆቦ ዙሪያ ቀበሌ ለሚያሠራው የንጋት መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የመስኖ መሰረተ ልማት ከደረጃ 3 እና በላይ ያሉትን WWC ሥራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች መምሪያው ባወጣው የመስኖ ግንባታ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳችሁን በቴክኒካልና ፋይናንሽያል በሚል ተለይቶ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በጥንቃቄ ሞልቶና በፖስታ አሽጎ በማቅረብ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

1.     በዘርፍ የተሰማሩና ሕጋዊ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ሰርቲፊኬት/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin number) ማቅረብ የሚችል

2.     ተጫራቾች ከደረጃ 3 እና በላይ የሆኑና የውሃ ሥራዎች /WWC/ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.     በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 2 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከቴከኒካል እና ፋይናሽያል መጫረቻ ሰነዶቻችሁ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

4.     ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በCPO በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂስ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ የተቆረጠ ደረሰኝ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች ዋጋ ሊሞሉ ማንኛውም ግብርና ታክስ አካቶ መሙላት አለባቸው፡፡

6.     ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው 10% ዋስትና በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው፡፡

7.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ከሆነ ለ60 ቀን የሚቆይ ሆኖ መሠራት አለበት።

8.     የጨረታ ሰነዱ በ19/7/2018 ዓ.ም እስከ 8/8/2018 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ የታደሰ ንግድ ፍቃዱን በመያዝ ባለቤቱ /ህጋዊ ውክልና ያለው በአካል ሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን በመቅረብ መግዛት የሚችሉ መሆኑን አውቀው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ዋጋ ሞልተው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9.     ጨረታው በ 9/8/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የማይገኝ ተጫራች በተገኙት ስምምነት ይከፈታል ባይገኝም በሕግ ተገዥ ይሆናል።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ የቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ የፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በሚል ተለይቶ ሁለቱም አይነት ፖስታ ላይ ንግድ ፍቃድና ቲን ነምበር ቫት አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት።

11. ተጫራቾች በሁሉም የጨረታ ሰነዳቸው ላይ ክብ ማህተምና ፊርማ መፈረም ይኖርባቸዋል።

12. ውድድሩ በሎት ወይም በድምር ዋጋ ስለሆነ ሁሉም የእቃ ዋጋ መሞላት አለበት።

13. የሳይት ምልከታ የሚደረግበት ቀን ጨረታው በዋለ በ7ኛው ቀን መሆኑ የተጠበቀ ነው።

14. አሸናፊው አካል በፍትሕ ውለታ በመወለድ በመያዝ ግዴታው መሆኑን ግንዛቤ መያዝ ይኖርበታል።

15. ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ በማንበብና በመረዳት ዋጋ መሙላት ይኖርባችኋል።

ማሳሰቢያ፡-

•        ቲን ነምበር፡ ንግድ ፈቃድ እና የቫት የምስክር ወረቀት ለየብቻ በአንድ አንድ ገጽ ኮፒ ተደርጎ መያያዝ አለበት።

•        መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

•        የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።

•        በውክልና ጨረታ ሰነድ የሚገዛ አካል ኦሪጅናል የፍትሕ ውክልና ይዞ መቅረብ ይኖርበታል ውክልናውም አቻና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።

•        በቴክኒካል መስፈርቱ 70% እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያመጣ አካል ብቻ ወደ ፋይናሻል ውድድር የሚገባ መሆኑ ይታወቅ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (0333311597/2680) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን

Save Tender