Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline05 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-05 00:00:00
  • Categories Equipment

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለፖሊስ ሠራዊት ቀለብ(ሬሽን) ዕቃ ግዥ በህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2018

 

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለፖሊስ ሠራዊት ቀለብ(ሬሽን) ዕቃ ግዥ በህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 የሠራዊት ቀለብ (ሬሽን)

በዚሁ መሰረት፡፡

1.       2018 ዓ/ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል

2.       አግባብ ካለው መንግስት ተቋም የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና ተጨማሪ ታከስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3.       የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለፖሊስ ሠራዊት ቀለብ(ሬሽን)ዕቃ ግዥ በህጋዊ ተጫራቾች ከአሰሪና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተጫራቾች በጨረታ ሠነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።

4.       ተጫራቾች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት(ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና(ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው። ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይሆናል።

5.       አንድ ተጫራች ከአንድ ሠነድ በላይ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።

6.       የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሎት1 (100,000) አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ወይም የክፊያ ማስያዣ(Cpo) ከማረጋገጫ ሠነድ ጋር ማቅረብ ሚችል/ትችል።

7.       ተጫራቾች በመመሪያው መሠረት ህጋዊ ፍቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ(VAT)የተመዘገበበት ሰርተፍኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአሥር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር ለሎት 1 300/ሦስት መቶ ብር/ በሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ግቢ ግዥ ንብረት ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 309 3ኛ ፎቅ በመክፈል ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

8.       የጨረታው ሠነድ ተጫራቾች በመመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ቴክኒካል ሁለት ኮፒ ሠነዱ በተለያየ በፖስታና ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በመጨመር በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (11ኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00-4፡30 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት 4፡30 ይታሸጋል።

9.       ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ የዛኑ እለት 4፡30 ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።

10.   የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሠዓት ይሆናል።

11.   ገዥ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

Save Tender