የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የመኪና አይነቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2018
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የመኪና አይነቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ተጫራች ሁሉ ከዚህ በታች በተግለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎች የተመዘገቡ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ለሚችሉ ሁሉ ክፍት ነው።
2. ተጫራቶች የመኪናዎቹን ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሆኖ የሚያቀርቡትን የመኪና ስፔስፊኬሽን የሚገልጽ ዝርዝር መግለጫ ካታሎማ በቴክኒካል ፖስታው ውስጥ አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢ.ቁ 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 2% በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ C. PO/ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው የቴክኒካሉን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ፋይናንሻሉን ሲፒኦውን ጨምሮ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ለየብቻ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 05 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታ ሰነዱን 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በይፋ ይከፈታል።
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ ኮምቦለቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስ.ቁ 033-551-02-72 በመደወል ወይም በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
