ገላን ሜታል ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር የተለያዩ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የማሸን ክፍሎች በቁርጥራጭ (Scrap) መልኩ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ገላን ሜታል ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ገላን ሜታል ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር የተለያዩ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የማሸን ክፍሎች በቁርጥራጭ (Scrap) መልኩ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል በመሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ቃሊቲ ውሃ ልማት አካባቢ በሚገኘው ቅጥር ግቢ በመምጣት በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በማየት የመወዳደሪያ ወይም የመጫረቻ ዋጋችሁን ማስገባት የምትችሉ መሆኑ እንግልፃለን።
1. የዘመኑ ግብር ከፋይ የሆነ፣
2. የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣
3. የግብር ከፋይ መለያ መረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን መጋቢት 17 እስከ መጋቢት 19 ቀን 2018 ጠዋት 3፡00 ሰዓት፣
5. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ነው በመሆኑ ከላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች የመግዣ ዋጋችሁን በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 መጋቢት 19/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ። ጨረታውን ተሳታፊዎች በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተከፍቶ አሸናፊ ከታወቀ በኋላ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት መጋቢት 18/2018 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።
አሸናፊውም ያሸነፈበትን መጠን ክፍያ ፈፅሞ እቃዎቹን በሶስት የስራ ቀን ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 439 2563 ወይም 09 66 27 24 44 በመደወል መረዳት ይቻላል።
ማሳሳቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ገላን ሜታል ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር
