በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበ ደብር ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት በገበያ ማዕከላት ሥራ የሚውል ግሬድ 75 ሜጋ ፖስካል የሆነ የቱርክ አርማታ ቶንዲኖ ብረት ግዥ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበ ደብር ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት በገበያ ማዕከላት ሥራ የሚውል ግሬድ 75 ሜጋ ፖስካል የሆነ የቱርክ አርማታ ቶንዲኖ ብረት ግዥ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. በዘርፋ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ሰርተፍኬት እና ማንነትን ሊገልጽ የሚችል የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል /የምትችል/።
2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ተያያዥ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በተጠቀሱት ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000,00 / አንድ ሺህ ብር / እየከፈሉ በቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰ/ጉ/አስ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች በዝርዝር ሰነዱ ላይ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በፖስታ አሽገው አንድ ላይ ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
5. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን ዋናውንና ቅጅ በማለት በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ሰነድ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በዕለቱ ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን እለቱ በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
7. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ በሰነዱ የተመላከቱትን ሁሉም የቱርክ አርማታ ቶንዲኖ ብረት አቅርቦቶች ፕሮጀክት ሳይቱ ከሚገኝበት ማለትም ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ድረስ በራሱ /በራሷ/ ትራንስፖርት የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ካለ ተቀባይነት የለውም።
9. የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 033-336-0021 ወይም 0912034009 መደወል ይቻላል።
የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ አስ/ጽ/ቤት
