Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግንባታ ዕቃዎች እና የተለያዩ የሴቶች ንጽህና መጠበቅያ ቁሳቁስ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

1)     ሎት አንድ Etiopia Human Capital Operation (HCO) ፕሮጀክት በጀት ለውሃ መስኖ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ለሴቶች /ህ/ጉ ጽ/ቤት እና ለትምህርት ጽ/ቤት የግንባታ ዕቃዎች ግዥ

2)     ሎት ሁለት Etiopia Human Capital Operation (HCO) ፕሮጀክት በጀት ለትምህርት ለሴቶች /ህ/ጉ ጽ/ቤት የተለያዩ የሴቶች ንጽህና መጠበቅያ ቁሳቁስ ዕቃዎች ግዥ

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት Etiopia Human Capital Operation (HCO) Tሮጀክት በጀት ለውሃ መስኖ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ለሴቶች ጽ/ቤት እና ለትምህርት ጽ/ቤት የግንባታ ዕቃዎች እና ለትምህርት: ለሴቶች ጽ/ቤት የተለያዩ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ከታች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታማሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡

1.     በዘርፉ የታደስ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት

2.     የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት

3.     የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው

4.     የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል

5.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ላት

6.     ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ/ነች

7.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8.     ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ዋና እና ኮፒውን በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሽገ በሁለት ወጥ ፖስታዎች ለየብቻ በማዘጋጀት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9.     ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ እንደተመለከተው ለሚጫረቱት ሰፒኦ cpo ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ ጨረታ ውድቅ ይደረጋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በ15ኛው ቀን ሎት አንድ በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል ሎት ሁለት በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡30 ላይ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

10. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይቻላል።

11. ጨረታ አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን ዕቃ ወይም ንብረት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ ማስረከብ ይኖርበታል።

1.      ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 ድረስ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን - ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ማሟላተ ይኖርባቸዋል፣ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን እንዲያቀርቡ የተጠየቁ ማስረጃዎችን ያላቀረበ እንደሆነ ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት ከውድድር ውጭ ይደረጋል።

 

ማሳሰቢያ

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 091040954

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender