የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና ሶፍትዌሮችን ለመግዛት ይፈልጋል።
Oromia Construction Authority (የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና ሶፍትዌሮችን ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም
የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻ'ን፡፡
1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው።
2. አግባብነት ያለውና ከጨረታው ዓይነት ጋር የሚጣጣም በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
3. በታክስ ባለሥልጣን የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
4. የግብር መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
5. የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥና ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችላቸው ሕጋዊ ማስረጃ አግባብነት ካለው የመንግሥት መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. የአቅራቢነት ምዝገባ ላይ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ያላቸው።
7. መ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/ በታች ማቅረብ አይቻልም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሆኖ ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 1,000.00 (አንድ ሺህ) ብር ብቻ በመክፈል ከመስሪያ ቤቱ ግዥ፣ ንብረትና ፋይናንስ አስተዳደር ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ለመጫረት ዋጋ ያቀረቡባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው።
11. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒዉን እንዲሁም የዋጋ /Financial proposal/ እና የቴክኒኩን /Technical proposal/ ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻም አራቱንም አንድ ላይ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የድርጅታቸውን ሕጋዊ ማህተም በማድረግ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
13. ዘግይቶ የሚመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
14. ተጫራቾች ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
15. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አ ን/ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሳርቤት በሚገኘው የመ/ቤቱ ግምጃ ቤት ገቢ ካደረጉ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
16. ባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
አድራሻ፡- አ/አ ሳርቤት፣ ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ የኦሮሚያ ቢሮዎች ያሉበት ግቢ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የግዥ ንብረትና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ነው።
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን
