Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
  • Address ምስራቅ ጎጃም ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0587760443
  • Website
  • Deadline07 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-07 00:00:00
  • Categories Water Construction Machinery And Equipment

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ዉሃ ጽ/ቤት ለሀገረሰላም ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የውሃ ግንባታ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 06/2018

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ዉሃ ጽ/ቤት ለሀገረሰላም ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የውሃ ግንባታ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

1.     ለ2018 ዓ.ም የታደሰና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያለውና ማስረጃ ማቀረብ የሚችል፣

3.     የግጞዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

5.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የኢትዮጲያ ብር ለሚወዳደሩበት ሰነድ በመግዛት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 መውሰድ ይችላሉ፡፡

6.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡

7.     ጨረታዉ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቁጥር 04 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታዉ በዚሁ ዕለት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ይከፍታል፡፡

8.     የጨረታ መክፈቻ ቀን ዝግ /በዓል/ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

9.     አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበው ውል መያዝ አለባቸው።

10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0587760443 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender