Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-05 00:00:00
  • Categories Equipment And Accessories , Equipment

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አገልግሎት እና እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፈርኒቸር፣ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል አገልግሎት የሚውል የፈተና ወረቀት ማስቀመጫ ካሣ፣ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል አገልግሎት የሚውል በድጋሜ የወጣ የፈተና ማሸጊያ ቁልፍ፣ የመኪና ዲኮር፣ በድጋሚ የወጣ የትምህርት መገናኛ አገልግሎት የሚውል ሞንታርቦ፣ ሚክሰር፣ ስፒከር እና ዋየርለስ ማይክራፎን፣ የ2018 ዓ.ም አመታዊ የቢሮ የግቢ ፅዳት አገልግሎት እና የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1.     በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤

3.     የግዥው መጠን ብር ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ መሆን አለባቸው።

4.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰዉን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6.     የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት፣ ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ፈርኒቸር 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር፣ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል አገልግሎት የሚውል የፈተና ወረቀት ማስቀመጫ ካሣ 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር፣ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል አገልግሎት የሚውል በድጋሜ የወጣ የፈተና ማሸጊያ ቁልፍ 20,000/ሃያ ሺህ/ ብር፣ የመኪና ዲኮር 10,000/አስር ሺህ/ ብር፣ በድጋሚ የወጣ የትምህርት መገናኛ አገልግሎት የሚውል ሞንታርቦ ሚክሰር ስፒከር ዋየርለስ ማይክራፎን 50,000 /ሃምሳ ሺህ /ብር፣ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የቢሮ የግቢ ፅዳት አገልግሎት 10,000/አስር ሺህ/ ብር፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች 10,000/አስር ሺህ/ ብር ግዥ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

8.     የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል።

9.     ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ብ/ክ/መ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል።

10.  የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

11.  ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አ/ብ/ክ/መ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 6267 / 058 320 9939 / በመደወል ማግኘት ይቻላሉ።

12.  ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ

Save Tender