የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለአ/ም/ከ/ትምህርት መምሪያ በደረጃ 8 ለተደራጁ ማህበራት የግንባታ ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግንባታ ጨረታ ጥሪ
የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለአ/ም/ከ/ትምህርት መምሪያ
1. Lot 1 ለገሮ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ብሎክ ግንባታ
Lot 2 ለገሮ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለት ብሎክ
Lot 3 ለገሮ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሶስት ብሎክ የመማሪያ ክፍል ግንባታ
4. Lot 4 ለአባያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የላብራቶሪ ግንባታ
5. Lot 5 የቤሬ ዕድገት በር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ
6. Lot 6 የገሮ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላብራቶሪ ቢሮ እና መከለያ ግንባታ (Rataining)
በደረጃ 8 በተደራጁ ማህበራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN No) ያላቸው የዘመኑን ግብር 2018 ዓም የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ከገቢዎች የ2018 ዓ.ም ክሊራንስ ማቅረብ
2. አቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል /online/
3. ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ጨረታ 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
4. የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል
5. አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር ከጨረታ ያሰርዛል፡፡
6. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአ/ም/ከ/ፋ/ፕ/ል/መምሪያ ቢሮ ቁጥር3 በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ እንድትገዙ እንገልፃለን።
7. ዋጋቸውን በማያሻማ መልኩ እንድታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡
8. የጨረታ ሠነድ የሚገባው ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት እስከ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ሲሆን ዕለቱ ቅዳሜ ፤ እሁድ ወይም ክብረ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይሆናል፡፡
9. የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሲሆን የሚከፈተው 4፡30 በከተማው በፋ/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
10. ተጫራቾቱ ጨረታ ዶክመንት /ቴክኒካልና ፋይናንሻል/ ኦርጅናልና ኮፒ 1 ኮፒ 2 እንዲሁ የጨረታ ማስከበሪያ በተለያዩ ፖስታ አድርገው በእናት ፖስታ አሽገው እንዲያቀርቡ ይፈልጋል፡፡
11. ውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል፤
12. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
13. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የውሉን 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
15. ተጫራቾች በእጃቸው ላይ ስራ ወስደው 85% ያላደረሱ በጨረታው መወዳደር አይችልም፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- 0468 81 43 53
የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
