Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት
  • Address , Phone: 0905115511
  • Website
  • Deadline24 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-24 00:00:00
  • Categories Safety Clothe And Shoes , Vehicle Spare Parts

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው መነፅር (የእይታ መሳሪያ፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ድብልቅ ገብስ እና ስንዴ (እህል ነክ)፣ የልብስ መስቀያ አሻንጉሊት፣ ኮስሞቲክስ፣ ሸቀጣሸቀጥ ልዩ ልዩ እና አዳዲስ አልባሳት በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 15/2018 ዓ.ም

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው መነፅር (የእይታ መሳሪያ፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ድብልቅ ገብስ እና ስንዴ (እህል ነክ) ፣ የልብስ መስቀያ አሻንጉሊት፣ ኮስሞቲክስ፣ ሸቀጣሸቀጥ ልዩ ልዩ እና አዳዲስ አልባሳት በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን።

1.     ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

2.     በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡

3.     የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡

4.     በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የእቃዎቹ አስመጪ ወይም የአስመጭ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም፣ ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

5.     በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ሲፒኦ በማሰራት ያስሩትንም ሲፒኦ በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

6.     በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ ለግልዕ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።

7.     አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተገለፀ በ3 /ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

8.     አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

9.     ከላይ በተ/ቁ 8 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

10.  ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡

11.  ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12.  ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመስከተ የጥሪ ማዕከሱን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደሙሱ መጠየቅ ይቻላል።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት

Save Tender