Tender Detail

Tender Details


የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ በ2018 በጀት አመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች 1ኛ. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 2ኛ. የህክምና ላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፤ 3ኛ ላብራቶሪ የህክምና መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ በ2018 በጀት አመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች 1ኛ. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 2ኛ. የህክምና ላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፤ 3ኛ ላብራቶሪ የህክምና መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋበዛል።

1.     በየዘርፉ አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / Tin Number/ ማቅረብ የሚችል

2.     የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3.     ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝርና ስፔስፍኬሽን ወይም ዝርዝር መግለጫ ጨረታ ሰነዱ ለእያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነድ በመግዛት መሳተፍ ይቻላል።

4.     የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ላይ የሚሸጥበትን ዋጋ በትክክል በመሙላት በጠቅላላ ከሞሉት ዋጋ ላይ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማሰብ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ መሂ 1 በመቁረጥ ከጨረታ ፖስታው ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።

6.     ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በመለየት በታሸገ ፖስታ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ አማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ የግዥ ቡድን ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።

7.     በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ጉዳዮች ካሉ ማብራሪያ ለመጠየቅ በስልክ ቁጥር- 033 311 52 20 ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

8.     ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝባዊ በዓል/ቅዳሜ እሁድ/ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ስዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

9.     ጨረታውን አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሚያቀርበው ቋሚ እቃዎች ላይ የ6 ወር ጋራንቲ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

10. የጨረታው አሸናፊ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ በሚመለከተው ባለሙያ እየተረጋገጠ በመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።

11. በመጫረቻ ሰነድ ላይ ከሰፈሩት የውል ቃሎችና ሁኔታዎች ጋር መሰረታዊ ልዩነት ያለው ሀሳብ ማቅረብ ከጨረታው ተሳታፊነት ያሰርዛል።

12. ኢንስቲትዩቱ ጨረታ አሸናፊ ከለየ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት መ/ቤቱ የሚገዛውን የእቃ ብዛት 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት ይኖረዋል።

13. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ያንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከእነቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ፣ አድራሻ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል። በነጠላ ዋጋ ላይ ሆን ተበሎ የተጋነነ ስርዝ ድልዝ ከጨረታ ተሳታፊነት ያሰርዛል።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የተጫራቾች መመሪያን ሳይገነጠል አያይዘው ማቅረብ ግዴታ ነው።

15. የጨረታ አሸናፊዎች የሚለዩት በነጠላ ውድድር ነው።

 

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ

Save Tender