በአብክመ ግብርና ቢሮ የዋናው ቢሮ ኃላፊ ቢሮ ኢንተርየር ሥራ ለማሠራት በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃ GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል
በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የግንባታ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ግብርና ቢሮ የዋናው ቢሮ ኃላፊ ቢሮ ኢንተርየር ሥራ ለማሠራት በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃ GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፤በመሆኑም
ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልበሥራና ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
የ2017 በጀት ዓመት ከግብር ነፃ መሆናቸውን እና በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፤
በክልሉ እና በቢሯችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ፤ ከቢሮ ጋር ሌላ ፕሮጀክት ያላቸው ከሆነ እየተከናወነ ያለው ሥራ 70 ፐርሰንት የደረሰ መሆን ይገባዋል።
የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ22ኛው ቀን ይሆናል።
ተጫራች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሳተፍበትን ቦታ በግልፅ በመጥቀስ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፣ የኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት።
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ለ21 ተከታታይ ቀን ከዋለበት በኋላ በ22ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ለ 60+28 ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና መቅረብ አይቻልም።
ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251-058 226-2891 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
