Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +2510582262801
  • Website
  • Deadline08 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-08 00:00:00
  • Categories Construction Works , Contractors

በአብክመ ግብርና ቢሮ የፍኖተ ሰላም ግብርና ፅ/ቤት እድሳትን በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋም ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት በጀት ለማሰራት በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃGC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል

በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ ግብርና ቢሮ የፍኖተ ሰላም ግብርና ፅ/ቤት እድሳትን በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋም ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት በጀት ለማሰራት በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃGC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፤በመሆኑም

ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ያለውና ማቅረብ የሚችል፤

የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልበሥራና ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የ2017 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን እና በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፣ በክልሉ እና በቢሯችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ መሆን ይገባቸዋል

የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ22ኛው ቀን ይሆናል።

ተጫራች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሳተፍበትን ቦታ በግልፅ በመጥቀስ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፣ የኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት፤

ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ለ21 ተከታታይ ቀን ከዋለበት በኋላ በ22ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ለ120 ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና መቅረብ አይቻልም።

ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251-058 226-2891 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬ

Save Tender