በጉለሌ ክ/ከተማ የማይጨው ጤና ጣቢያ የላቦራቶሪ እቃዎች የመድሃኒት የደንብ ልብስና የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ እያንዳንዱ የጨረታው ተሳታፊ የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያ ነጥቦችን በመረዳት ሰነዶች ላይ እንዲያሟሉ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ የ ማይጨው ጤና ጣቢያ
ኢ/ህ/ክ/መንግሥት በቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 8 posted
የጨረታ ማስታወቂያ (1)
በጉለሌ ክ/ከተማ የማይጨው ጤና ጣቢያ የላቦራቶሪ እቃዎች የመድሃኒት የደንብ ልብስና የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ እያንዳንዱ የጨረታው ተሳታፊ የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያ ነጥቦችን በመረዳት ሰነዶች ላይ እንዲያሟሉ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
4. የግብር ከፋይነት ቲን ነበር ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው
5. የምዝገባና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር04 \የእለት ገንዘብ ተቀባዮች ጋር በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ ብር100.00/አንድ መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
6.ተጫራቾች የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋ እና ቫትን ጨምሮ ጠቅላላ ዋጋው በግልጽ ማስፈር አለባቸው፡፡
7.ተጫራቾች ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር/10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የሚያቀርቡትን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም (CPO) እራሱን በቻለ በተለያየ ፖስታ ለየብቻው በማሸግ በተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪ ለደንብ ልብስ ጠቅላላ ዋጋ 2000/ሁለት ሺህ ብር/ ለመድሃኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንት/5000/ የኔትወከ እቃዎችservice/maintenance fee computer, printer, laptop and scanner equipments/5000/የጭነት አገልግሎት /ትራንስፖርት /3000 በባንክ በተመሰከረለት (CPO) / በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው
8.በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 10ኛው ቀን እስከ ከሰአት 11፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 407 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታውም በ1ዐኛው ቀን ከሰአት 11፡00 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፡፡
9.ጨረታው በዘኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 3፡00 በማይጨው ጤና ጣቢያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
10.ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ እንዲያስገቡ ሲጠየቁ በወቅቱ በራሳቸው ትራንሰፖርት እስከ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል አዲሱ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11.መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ የመብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ከጨረታው መከፈቻ ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቶች ባቀረቡት ናሙና የጨረታ ኮሚቴው በጥራትና በዋጋ የተሻለውን ይመርጣል ናሙና ያልቀረበበት ዕቃ ከውድድርውጪ ይሆናል፡፡
13.የተጫራቾች ሙሉ ስማቸው አድራሻቸውንና ፊርማቸውን እና ማህተማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
14.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው ሎት እንደሚወዳደሩ በግልፅ ለይተው መፃፍ አለባቸው፡፡
15. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለናሙና ያቀረቡትን እቃ በጊዜ ካልወሰዱ ከ6ወር በላይ ከቆየ ለመንግስት ውርስ ይደረጋል፡፡
16.ተጫራቾች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ወይም ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
17.ጨረታን ማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
18.ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
19.ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህ ባይሆን ግን በጨረታው የተያዘው ቼክ ወይም ሲፒኦ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
20 ማንኛውም ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋው ማቅረቢያ ሰነድ ላይቫትን አካቶ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን ተጫራቹ እንዳካተተ ይቆጠርለታል
21. ጤና ጣቢያው ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከውል በፊት እስከ 20% መጨመርወይም 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
22. በግምገማ ወቅት አኩል ውጤት ያመጡ ተወዳዳሪዎች በእጣ የሚለዩ ይሆናል ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራች ለሚወዳደርበትን እቃ ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም ለግዥ ፈጻሚው መ/ቤት የተጻፈ ደብዳቤ በመያዝ በሚያመርቱትና እሴት ለጨመሩበት ላይ ብቻ 3% ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡
አድራሻ 6ኪሎ ኢንተርናሽናል ሊደር ሽኘ ኢንስቲትዩት አለፍ ብሎ ግብፅ ኤንባሲ ፊት ለፊት ወይም
በስልክ ቁጥር-0111-54 20-68 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ የ ማይጨው ጤና ጣቢያ
