በደ/ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዘመን በማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት በከተማው መሠረተ ልማት ፕሮግራም የተለያዩ ግንባታዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዘመን በማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት በከተማው መሠረተ ልማት ፕሮግራም
LOT: 1 የዲች ኪዳን (Ditch Cover) ግንባታ ሶስት ክ/ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ያለው
LOT: 2 የጠጠር መንገድና ዲች ግንባታ (Gravel Road & Drainage Work) ከአጠድሳ ቁጤባ ቤት እስከ ኡሉለ ወንዝ ድረስ ያለው
LOT 3 የጠጠር መንገድና ዲች ግንባታ (Gravel Road & Drainage Work) ከሱማሞ መንገድ እስከ ኡሉሌ ወንዝ ድረስ ያለውን ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፦
1. በኮንስትራክሽን ቢሮ የተመዘገበ ሎት -1 ደረጃቸው GC/BC-5 እና ከዚህ በላይ እና ለሎት-2 እና 3 ደረጃቸው GC/BC-8 የበቃ ማህበር ሆኖ በአከባቢ የተደራጁ ማህበራት ብቻ
2. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው እና ኦሪጅናል መረጃ ማቅረብ የሚችል
3. የ2018 ዓ. ም ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ እና ክሊራንስ ያለው
4. በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
5. ቲን ሠርቴፊኬት ያለው
6. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
7. ማህበር ከሆነ ወቅታዊ የደረጃ ዕድገት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
8. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
9. በOnline አቅራቢነት E-GP የተመዘገበና ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል ፤
10. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት-1 450,000 (አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ ፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: _ ለሎት- 2 እና 3 አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለዋስትና ካቀረቡት ጠቅላላ 3% ከኦሞ ባንክ ሌሎች ባንኮችና ማይክሮ ፋይናንስ ዋስትና (CPO) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
11. ተጫራቹ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአረካ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ማዕከል በመግዛት የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም የታሸገ ፖስታ በማሸግ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ31ኛው ቀን ዕለቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
12. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፍል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ተጫራቾች ያለመገኘታቸው የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም።
ለበለጠ መረጃ በሊቁ 0913 055 185 ላይ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
ከወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
